ጕግፈኛ ወሮበላ ኮሎንያል ጣልያን ኢትዮጵያን ስበህገወጥ ሲወር፣ ጀግና በላይ ዘለቅ ዘራፍ ብሎ በaaርበኝነት የተታገሉ ጀግና ኢትዮጲያዊ ነበሩ። ኮሎንያል ጣልያንን በጅግነንትና በኣርበኝነት የመከቱ ኣንደኛ ታሪከኛ ኢትዮጵያዊ ናቸው። በኣሁኑ ውቅት ግን “ኢትዮጵያ ጀግና ኣልወለደችም” እየተባለ ሲወራ ነው የሚሰማ። ጀግናው በላይ ዘለቀ ከአባታቸው ከባሻ ዘለቀ ላቀው እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ጣይቱ አስኔ  በ1904 ዓ.ም ተወለዱ።

ስለ ትውልድ ቦታቸው ብዙ አወዛጋቢ የሆኑ የተለያዩ መረጃዎች ቢኖሩም ፣ በተወለዱ በአራት ዓመታቸው አባታቸው ባሻ ዘለቀ ላቀው የልጅ እያሱ ባለሟል ሆነው የአንድ ክፍለ ጦር ኃላፊ ስለነበሩ ልጅ እያሱ በተያዙ ጊዜ ከዚያ አምልጠው በቦረና ሳይንት አውራጃ በጨቃታ ወረዳ ልዩ ስሙ ጣቀት መድሉ ከተባለው ቀበሌ ተቀምጠው እንዳሉ ከአንድ ሰው ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው በፀብ መካከል የሰው ህይወት ያልፍባቸዋል። ለዚህም ምክንያት ወሎን ለቀው ወደ ጐጃም መጡ። ጐጃምም በተለይ በቢቸና አውራጃ በእነማይ ወረዳ ልዩ ስሙ ለምጨን ከተባለው ቀበሌ ተቀመጡ። ብቸና ውስጥም ተቀምጠው ሳለ እርሳቸውን የሚያስስ ልዩ ጦር በጥቆማ ወደ አካባቢው ተላከ። ከዚህ ጦር ጋርም ከፍተኛ ውጊያ ተደረገ። በዚህ ውጊያ ወቅት በላይ ዘለቀ እና እጅጉ ዘለቀ ልጆች ቢሆኑም ተኩሱን እያዩ የሚወድቁትን ጥይቶች ይቆጥሩ ነበር። ከውጊያው በኋላም የበላይ ዘለቀ አባት ተመተው ይወድቃሉ። ይሞታሉ።

ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ውለታ የፈጸሙ፣ ጀግናንና ልበሙሉነት የነበራቸው ኢትዮጵያዊ በላይ በላይ ዘለቀ፣

እነ በላይ ዘለቀም ካለ አባት ከእናታቸው ከወ/ሮ ጣይቱ አሰኔ ጋር ማደግ ይጀምራሉ። ከፍ ሲሉም የአባታቸውን ገዳይ እና አስጠቁሞ እየመራ ያስገደላቸው ማን እንደሆነም ለማወቅ ማሰስ ጀመሩ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሳሉ ፋሺስት ኢጣሊያ በ1928 ዓ.ም ኢትዮጵያን ወረረች። በላይ ዘለቀ በወቅቱ የ24 ዓመት ወጣት ነበሩ። ሀገርን የወረረውን የኢጣሊያን ጦር ለመውጋት ቆርጠው ተነሱ። በወቅቱ ከ200 እስከ 300 ያህል ጦር በስራቸው ሊያሰባስቡ ቻሉ። በወቅቱም የአካባቢውን ሕዝብ ሰብስበው የሚከተለውን ንግግር አደረጉ።

“እኔ የዘለቀ ልጅ የምታዩትን የአባቴን አንድ ጥይት ጐራሽ ናስማስር ጠብመንጃዬን ይዤ በሀገር በረሃ የአላዩን ወንዝ ይዤ፣ የአለቱን ድንጋይ ተንተርሼ፣ አሸዋውን ለብሼ ዋሻውንና ተራራውን ምሽግ አድርጌ የመጣውን ጠላት እቋቋመዋለሁ፤ እንጂ እንኳንስ እናንተ የእናቴ ልጆች እጅጉ እና አያሌው ጥለውኝ ሄደው አንድ እኔ ብቻ ብቀርም ከዓላማዬ ፍንክች አልልም። እናት ሐገሬ ኢትዮጵያ ስትደፈር ከማየት ሞቴን እመርጣለሁ። የፈራህ ልቀቀኝ! ለውድ እናት ሀገርህ መስዋዕት ለመሆን የምትፈልግ ሁሉ እኔን ተከተለኝ”

 በዚህን ጊዜ የኒህን ጀግና ልበ ሙሉነት የተረዱት ከ150 ያልበለጡ አገር ወዳጆች ሲቀሩ ሌሎች ለጠላት እየሄዱ ገቡ በላይ ዘለቀ ጐጃም ውስጥ የጠላት ጦር መቆሚያ እና መቀመጫ እንዳይኖረው በማድረግ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ውለታ ያበረከቱ ጀግና ናቸው። ለምሳሌ ለምጨን ከተባለ ቦታ በግንቦት ወር 1928 ዓ.ም ከኢጣሊያ ፋሽስት ጋር ገጥመው ሲዋጉ ከወገን በኩል በመጠኑ የቆሰለና የሞተ ሲኖር ከጠላት በኩል በብዛት ሞቶበት በመጠኑ ስለቆሰለበት በዚሁ ዕለት ድል አድርገዋል። ከዚህ ቀጥሎም ቀኛዝማች ሰማነባዋ የተባሉት የኢጣሊያ የባንዳ አለቃ ስለነበሩ በቂ መሣሪያ እና ወታደር ስጠኝ እና በላይ ዘለቀን ሲሆን ከነ ነፍሱ እጁን ይዤ አለበለዚያም አንገቱን ቆርጬ በሦስት ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ አመጣዋለሁ፤ ለወንድነቱ እኔ አለሁ፤ ለበረሃውም እኔው ነኝ፤ በማለት ሊፈፅሙት ያልቻሉትን ተስፋ ለኢጣሊያ ፋሽስት ሰጥተው በትምክህተኝነት ፎክረው የተሰጣቸውን 500 ወታደር ይዘው በላይ ዘለቀን በመውጋት በቢቸና አውራጃ በሸበል በረንታ ወረዳ ልዩ ስሙ አባራ ጊዮርጊስ ከተባለው ቦታ እንደደረሱ በላይ ዘለቀ ያለበትን አሳዩኝ፤ እናንተ እያበላችሁ እያጠጣችሁ ነው ያጐለበታችሁት በማለት በሚስቱ እና በከብቱ ላይ በሚያሰቃዩበት ጊዜ በላይ ዘለቀም ከለምጨን ተነስተው በየረባቲ በተባለ ቦታ አድርገው ሲሄዱ ህዝቡን የሚቀሰቅስ ሽለላ አሸልለዋል።

የጀግና በላይ ዘለቀ ሽለላ።

“ባላገር ተነሳ ያገር ልጅ ተነሳ፣

ፈረንጅ ቀቅሎ ሳያደርግህ ማርሳ።

ያባትህን ጋሻ ጦርህን አንሳና ተነሳ፣

ያገሬ ልጅ አገርህን አቅና።

እንኳንስ ኢጣሊያ ቢመጣ ፈረንጅ፣

አትሆንም ኢትዮጵያ ያለ ተወላጅ።

ጥንት አባቶቻችን በጦር በጐራዴ ሲዋጉ በጋሻ ፣

ለኛ አውርሰውናል እስከመጨረሻ።

አድዋን አስታውሰው! የምኒልክን ቦታ፣

እኛ አንበገር ከንቱ አትንገላታ።

 

መርባብ ሓበሬታ ደቀባት.ኮም  30. መስከረም 2017 ዕ.ም.ፈ.